Okebiz Video SearchTitle:አባ ጳውሊ ከሰይጣን ጋር ያደረጉት ቃለ መጠይቅ
Duration:34:02
Viewed:241,817
Published:09-05-2020
Source:Youtube

ሳጥናኤል ከሰው ልጆች መሀከል የሚወደውና የሚጠላው እንዳለ ተናግሯል በሳጥናኤል ዘንዳ የምንወደድ ..ወይም እንድንወደድ የምንፈልግ ስንቶቻችን እንሆን ….. ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ትሆኑ ዘንድ ጋብዘናቹሀል መልካመ ቆይታ
ሰይጣን በአባ ጳውሊ ተገዝቶ ሳለ ያወጣው ምሥጢር

ከዚህም በኋላ አባ ጳውሊ ‹‹ሰዎች ፈጣሪያቸውን እንዲክዱ የምታደርገው በምን መንገድ ነው?›› አለው፡፡ ዲያብሎስም ‹‹ነዚህ ዓለም የማደርገውን ሁሉ ነገርኩህ፤ መጀመሪያ ልጆች የወላጆቻቸውንና የአሳዳጊዎቻቸውን ምክር እንዳይሰሙ ለቃላቸውም እንዳይታዘዙና ‹እናንተ ይልቅ በእውቀት እኛ እንበልጣለን፣ እኛ እናውቃለን› እንዲሉ እናደርጋቸዋለን፡፡ ዳግመኛም ወላጆቻቸውንና በዕድሜ የሚበልጧቸውን እንዲሳደቡ እናደርጋቸዋለን፡፡ በዚህም ምክንያት የቤተሰብ ፍቅር እናሳጣቸዋለን፡፡ በየሄዱበት ሁሉ እንደተረገሙ ይኖራሉ፡፡ ከዚህም በኋላ በክህደት፣ በዝሙት፣ የምንዝር ጌጥን በመውደድ፣ በስካር፣ በስርቆት፣ ነፍስን በመግደል ፈጽመው እንዲወድቁ እናደርጋቸዋለን፡፡ በመጨረሻም ተስፋ ቆርጠውና አእምሮአቸውን አጥተው ቁጥር የሌለው ኃጢአትን እንዲሠሩ እናደርጋቸዋለን›› አለው፡፡

ዳግመኛም አባ ጳውሊ ‹‹እናንተ አሳቾች እንደሆናችሁ ለሰው በምን ትታወቃላችሁ? መጨረሻችሁስ እንዴት ነው?›› አለው፡፡ ዲያብሎስም ‹‹እንደ አንተ ንጹሕ የሆነ ሁሉ በሥራዬ ያውቀኛል፤ ኃጥአን ግን ሽታዬን ለይተው ሊያውቁኝ አይችሉም፡፡ ለጥቂት ደጋጎች ነው እንጂ ለሁሉ አንታወቅም፣ በመጨረሻ ሥራችን ግን እንተወቃለን›› አለው፡፡

አባ ጳውሊም ‹‹በዕድሜ ያረጀ ዘመኑም የተቃረበና ሥጋውም የደከመን ሽማግሌ በምን ትፈትኑታላችሁ?›› ብሎ ሲይቀው ዲያብሎስም ‹‹እኛ በሽማግሌዎች ብዙ ምክንያት እናገኛለን፡፡ ስንፍና እናመጣባቸዋለን፡፡ ጾም ጸሎትን እንከለክላቸዋለን፡፡ ዘመናቸውን እስኪረግሙና ራሳቸውን እስኪያጠፉ ድረስ የሚያደርስ ጥርጣሬን እናመጣባቸዋለን፡፡ ክፉ ሀሳብና ገንዘብ መውደድን፣ ሰላም ማጣትን፣ ተስፋ መቁረጥን በውስጣቸው እናደርጋለን፡፡ ከልባቸው የሕሊና ጸሎትን ከአንደበታቸው ምስጋናን እናጠፋባቸዋለን›› አለው፡፡


ቀጥሎም አባ ጳውሊ ‹‹እንዴት አድርገው ነው በገዳም ከሚኖሩት ጋር የምትዋጋው?›› አለው፡፡ ዲያብሎስም ‹‹አስቀድመን መነኮሳትን የምንዋጋው በገዳሙ ቆይታ ላላቸው ትላልቅ አባቶች እንዳይታዘዙ ለማኅበሩ አባት እሽ በጄ ብለው ምክራቸውን እንዳይሰሙ እናደርጋቸዋለን፡፡ እኔ የምነግራቸውንና የማሳስባቸውን ለአበው እንዳይነግሩ በማድረግ ነው፡፡ ዳግመኛም ጥርጣሬን እናመጣባቸዋለን፡፡ በሐሰተኛ ሕልም እናስታቸዋለን፡፡ በዚህ ባያምኑና ቢያሸንፉን ሌላ ብዙ የምኞት ፈተና እናመጣባቸዋለን፡፡ ገንዘብ መውደድን፣ የላመ የጣፈጠ መብላት መጠጣትን እናስመኛቸዋለን፡፡ ያለምክንያት በየጊዜው ሴቶች ወንዶችን ወንዶችም ሴቶችን እንዲያዩና እንዲገናኙ እናደርጋቸዋለን፡፡ በዚህም በእነርሱ ላይ ታላቅ ውድቀትና አእምሮ ማጣትን እናመጣባቸዋለን፡፡ የማይጠቅም ዙረትን እንዲያበዙ እናደርጋቸዋለን፡፡ ሰውን የሚያጣሉና ነገር አመላላሾች እንዲሆኑ የአባቶችን ምክር እንዳይሰሙ፣ ሥራን እንዳይወዱ በአኗኗራቸው በአንድ ቦታ እንዳይጸኑ እናደርጋቸዋለን፡፡ በአፋቸው ‹እኛ ዓለምን ንቀናል› እንዲሉ ነገር ግን የዓለም ፍላጎታቸው በላያቸው በዝታ እንዲትታይና መንፈሳዊ ዕውቀትን ትዕግስት መረጋጋትን እንዲያጡ እናደርጋለን፡፡ ከገዳማቸው በወጡ ጊዜ ከገዳማቸው ልቡናቸውን እናርቃለን፣ እኛ የዚህን ዓልም ሥራ ስለምናሳምርላቸው በስም መነኮሳት ሲባሉ በገዳም መኖራቸውን ፈጽመው ይጠላሉ፡፡ በዚህ ሁሉ ፈትነናቸው ቢያሸንፉን ሌላ የሚፈተኑበትን መንገድ እናመጣባቸዋለን፣ ሌላው በሚሠራው ሥራ በቅናትና በቂም እንዲነሡና ሌላውን እንዳይሠራ እንዲያውኩት እናደርጋቸዋለን፡፡ በመሠሩት በማንኛውም ሥረራ ውዳሴ ከንቱን እንዲፈልጉና ራሳቸውን ክፍ ከፍ እንዲያደርጉ ሌላውንም እንዲነቅፉ እናደርጋቸዋለን›› አለው፡፡

አባ ጳውሊም ‹‹በዚህ በምታመጣባቸው መከራ ምን ትጠቀማለህ? እነርሱስ በምን ያሸንፉሃል?›› አለው፡፡ ዲያብሎስም ‹‹ፈጣሪያቸውን እንዳያመሰግኑና ተስፋ እንዲቆርጡ ከዘላለም ሕይወት እንድናቸጠፋቸው እንወዳለን እንጂ የምናቀገኘው አንዳች ጥቅም የለንም፡፡ ‹በምን ያሸንፉሃል?› ስለምትለኝም በመታዘዝና በትዕግስት፣ በጾምና በጸሎት፣ በቂም በቀል ንጹሕ በሆነ ልቡና ባለመለያየት ወንድሞቻቸውን ፍጹም በመውደድ፣ ከዚህ ሁሉ ጋራ ትሕትና ከመንፈሳዊ ሥራቸው ሁሉ ትበልጣለችና በፍጹም ሃይማኖት ትሕትናን ቢይዙ ያሸንፉናል፡፡ በመጨረሻም የክርስቶስ ሥጋና ደም የእኛን መርዝ ያጠፋልና እሾሃችንንም ይነቅላልና ያቃጥላል›› አለው፡፡ እዚህ ጋር ቅድስት እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ገድል ላይም ያገኘነውንም ነገር ልናካፍላችሁ ወደድን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ እርሷም የዲብሎስን የማሸነፊያ መንገዶች መርምራዋለች፡፡ ቀጥሎ በዝርዝር እንመልከተው፡፡

ሰይጣን የሚሸነፍባቸውን ሦስት ዋና ዋና መንገዶች ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እንደነገራት፡- ‹‹ከዕለታትም በአንደኛው ቀን እናታችን ክርስቶስ ሠምራ ዕለተ ሞቷን እያሰበች በጣና ባሕር ውስጥ ቆማ ስታለቅስና ስትጸልይ ሣለች ዲያብሎስ በሊቀ ጳጳሳት ተመስሎ እጅግ አስደናቂና ግሩም በሆነ አርአያ ወደ እርሷ መጣ፡፡ እርሷም ልትሰግድለት ወደደች፣ ከኃዘኗ ያረጋጋት ዘንድ ከቅዱሳን አንዱ የመጣ መስሏት ነበርና፡፡ ነገር ግን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ደረሰና ‹ይህ ሰይጣን እንጂ ጳጳስ ወይም ከቅዱሳን አንዱ አይደለምና አትስገጂለት› ብሎ ወደኋላዋ መለሳት፡፡ ዳግመኛም ‹አሁንም እንደልማድሽ ሂጂና ጠይቂው ማን እንደሆነ ይነግርሻል› አላት፡፡ በዚህን ጊዜ ወደ እርሱ ሂደችና ‹እሰግድልህ ዘንድ አንተ ማን ነህ?፣ ስምህስ ማን ይባላል?› ስትል ጠየቀችው፡፡ እርሱም ‹የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ› አላት፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከእርሷ ጋር እንዳለ አላወቀም ነበርና፡፡ እርሱ በእርሷ ላይ ተንኮል ለመሥራት እንደተራቀቀ ሁሉ እርሷም ነቃችበት ተራቀቀችበት፡፡ ቀጥሎም ‹እንግዲያውስ አንተ ሚካኤል ከሆንክ እስቲ ስለ ጽድቅ ነገር አስተምረኝ› አለችው፡፡ በዚህም ጊዜ ፈጽሞ ተደሰተ-ከዓላማዋ አሳስቶ በእጁ የገባችለት መስሎታልና፡፡ እንዲህም አላት፡- ‹ለምን ሰውነትሽን ታደክሚዋለሽ? ከዛሬ ጀምሮ ከዚህ ኃላፊ ዓለም ድካም ማረፍ ያስፈልግሻል፣ መጾምና መጸለይስ ለምን ይጠቅምሻል? በባሕርስ ውስጥ ቆሞ መጸለይና ሰውነትን ማድከም ማን አስተማረሽ?› አላት፡፡ በዚያን ጊዜ ‹አንተ የምትለውና መጻሕፍት የሚናገሩት የተለያየ ሆነሳ!?› አለችው፡፡ እርሱም ‹ማነው የለያየን?› አላት፡፡ እርሷም ‹ከአነጋገርህ የተነሣ እኔ ለየኋችሁ› አለችው፡፡ እርሱም ‹እስኪ ልዩነታችንን ንገሪኝ?› አላት፡፡ እርሷም ‹መጻሕፍት የጾመ፣ የጸለየ፣ የለመነም ሁሉ ፍጹም ዋጋውን ያገኛል ይላሉ፡፡ አንተ ግን አትጹሙ፣ አትጸልዩ ትላለህ› አለችው፡፡ ይህንንም ባለችው ጊዜ በእርሷ ላይ ፈጽሞ ተቆጣ፣ እጅግም አድርጎ አስደነገጣት፡፡ ዳግመኛም መለሰችና ‹በምን ትሸነፋለህ?› አለችው፡፡ አሁንም ቁጣውን አወረደባት፡፡ በሦስተኛው ጊዜ ከተቆጣ በኋላ ‹በእነዚህ በሦስቱ ነገሮች እሸነፋለሁ› ሲል መለሰላት፡፡ ‹አንደኛ ማንኛውም ሰው በዚህ ዓለም በሚኖርበት ጊዜ ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት እንግዳ ተቀብሎ የሚያስተናግድ፤ ሁለተኛው በራሱ ላይ ችግርና መከራ በመጣበት ጊዜ መከራውን ታግሦ የሚኖር፤ ሦስተኛው ቀድሞም ከመሬት የተገኘሁ ነኝ፣ ኋላም ተመልሼ ወደ መሬት እገባለሁ እሞታለሁ እፈርሳለሁ ብሎ በማሰብ ትሕትና የሚሠራና የመሳሰሉትን ሁሉ የሚያደርግ እርሱ ፈጽሞ ያሸንፈኛል› አላት፡፡ ይህንንም ከተናገረ በኋላ ክንፉን እያማታ ወደ አየር በረረ፡፡ እርሷም ከግርማው የተነሣ ፈጽማ ደነገጠች፣ በመሬትም ላይ.............................................

SHARE TO YOUR FRIENDS


Download Server 1


DOWNLOAD MP4

Download Server 2


DOWNLOAD MP4

Alternative Download :SPONSORED
Loading...
RELATED VIDEOS
ኑ ገነትንና ሲኦልን ሳንሞት ጎብኝተን እንምጣ (ራእየ ማርያም) ኑ ገነትንና ሲኦልን ሳንሞት ...
46:04 | 126,049
ዘላለማዊ ምክር ከማማ ልጣሽ ጠጅ ቤት  ፍራሽ አዳሽ 11 - ተስፋሁን ከበደ- ጦቢያ  S2Ep1 2@Arts Tv World ዘላለማዊ ምክር ከማማ ልጣሽ ...
27:47 | 516,302
በሌሊት የሚበሩ የእመቤታችን እርግቦች በሌሊት የሚበሩ የእመቤታችን...
13:36 | 622
የኅዳር ሚካኤል ወረብና ምልጣን -Hidar Michael Wereb በርእሰ ደብር ብርሃኑ አካል የኅዳር ሚካኤል ወረብና ምል...
27:58 | 17,707
ፀበላቸውን ከጠጣችሁ ስጋችሁ አይፈርስም ፀበላቸውን ከጠጣችሁ ስጋችሁ...
16:12 | 874
ሁሉ ባንተ ነው ሁሉ ባንተ ነው
13:21 | 277,124
እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ……..?                የሱ ፍጡር ያልሆናቸሁ ማድመጥ አለባችሁ እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ……..? ...
23:54 | 28,921
ቴክ ቶክ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ልዩ ቆይታ ክፍል 1/Tech Talk With Solomon Doctor Abiy Interview Part 1 ቴክ ቶክ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ...
44:16 | 183,491